የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለተከበራችሁ የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀፅ 366፣367፣370 እና 372 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀፅ 19 መሰረት የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 18/2018ዓ/ም ከጠዋቱ 03፡00 ሰኣት ጀምሮ በራስ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባኤው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

  • የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡ በማይክሮ ፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር
  • የማህበሩ የተፈረመ ካፒታል 32,005,000
  • የማህበሩ የተከፈለ ካፒታል 32,005,000
  • የማህበሩ የምዝገባ ቁጥር  MT/LA/3/0057667/2016
  • የማህበሩ ድረ -ገፅ  www.tiritmicrofinance.com
  • የማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ አ/አ ከተማ – ለሚ ኩራ ክ/ከተማ – ወረዳ 08-4E ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎች

የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ

  1. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ
  2. እ.ኤ.አ የ2024/2025 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ
  3. እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 /2024/2025  የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ
  4. እ.ኤ.አ የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የተገኘው ኪሳራ/ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን
  5. እ.ኤ.አ የ2025/2026 የውጭ ኦዲተር ሹመትና አበላቸውን መወሰን
  6. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ

የ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ማሳደግ
  2. አክሲዮን ማህበሩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *