የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ።
የስብሰባ ጥሪ
ለጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ
ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ
የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366 (1)፣ 367 (1 እና 2)፣ 370፣ 371፣ 372 እና 393 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 15፣16፣17፣18፣19 እና አንቀጽ 23 ድንጋጌዎች መሰረት ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ሰሚት ሳፋሪ ሰኒ ሳይድ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል። ስለሆነም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን ሰዓት እና ቦታ ተገኝታችሁ በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል።
የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ካፒታል፡ ብር 32,005,000.00
የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈል ካፒታል: ብር 25,752,000.00
የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር: MFI/068/2024
የአክሲዮን ማህበሩ የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር አዲስ
የአክሲዮን ማህበሩ የድህረ ገጽ አድራሻ፡ www.tiritmicrofinance.com
1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
- የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና የአገልግሎት ክፍያውን መወሠን
- ተፈርመው ያልተከፈሉ አክሲዮኖችን በሚመለከት ዉይይት ማድረግ እና ዉሳኔ ማሳለፍ እና
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው።
1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
- የማህበሩን ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ማሳደግና ቀጣይ የማህበሩን አቅጣጫ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ
ማሳሰቢያ
- ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ለመገኘት ማንነታቸውን እና ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ዋናውን ከፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፣
- በጉባኤው በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች እስከ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የማህበሩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ የውክልና ቅፅ በመሙላት በተወካያቸው አማካኝነት በስብሰባው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የውክልና ሰነዱን ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የወካያችሁን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
የጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ